እኔን ከጠየቃችሁ ግን ነገሩ ምንም ትርጉም የለውም። ሰዎች በእቃው ላይ እንዲረግጡ ካልፈለጋችሁ፣ በትልቅነቱ ሰርታችሁ ጠባብ መተላለፊያ መሃል ላይ አታስቀምጡት። አንዳንድ ጊዜ በዚህ የይዘት ማምረቻ ማሽን ውስጥ አለመግባት ይከብዳል። “ይህ ጉዳይ ፋይዳ የለውም” ማለት እንኳን ለሌሎች ሰዎች “አይ ፋይዳ አለው” የሚል ክርክር እንዲጀምሩ እድል ይሰጣቸዋል። ለአብነት ያህል አርሰናል ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ መድረሱን ያከበረበትን መንገድ መመልከት ይቻላል። እዚህ ጋር “የአከባበር ፖሊሶች” ብቅ ይላሉ። እነዚህ ወገኖች አንድ ክለብ ምን ያህል መደሰት እንዳለበት ወሰን ያስቀምጣሉ።
አርሰናል ጨዋታውን አሸንፎ ተጫዋቾቹ ደጋፊዎቻቸውን ሲያመሰግኑ፣ ርችቶች ሲተኮሱ እና ደጋፊዎች በስታዲየም ዘፈን ሲዘፍኑ፣ “ገና ምንም ሳያሸንፉ እንዲህ መሆኑ ከልክ ያለፈ ነው” የሚሉ ትችቶች መምጣት ጀመሩ። “ገና ለግማሽ ፍፃሜ ድል አውቶቡስ ላይ አይወጣም፣ አሳፋሪ ነው” የሚሉ ድምፆችም ተሰምተዋል። ቢቢሲ ስፖርት “የአርሰናል ደስታ ተገቢ ነበር ወይስ ከልክ ያለፈ?” የሚል ፅሁፍ አወጣ። ዌይን ሩኒ በፕራይም ቪዲዮ ላይ “እዚህ ደረጃ መድረስ ይገባቸዋል፣ ግን ገና ዋንጫውን አላነሱም። አከባበሩ ትንሽ የበዛ ይመስለኛል” ብሏል። በሌላ በኩል ኢያን ራይት “የአከባበር ፖሊሶች በብዛት ይወጣሉ። አትሰሟቸው! በእግር ኳስ ውስጥ እንደዚህ ያሉ ወቅቶችን መደሰት ያስፈልጋል” ሲል ተከላክሏል። በቶክ ስፖርት ላይ ጋቢ አግቦንላሆር ስለ ርችቱ ጥያቄ ሲያነሳ፣ አንድ የአርሰናል ደጋፊ “አንተ ጎበዝ ስላልነበርክ ርችት ተተኩሶልህ አታውቅም” በማለት በስልክ ተሳልቆበታል።
እኔ በበኩሌ በሽንፈት ወቅት የሚፈጠርን ቁጭት በመፍራት ርችት ለመግዛት እሰጋለሁ። በአውሮፓ ስታዲየሞች ውስጥ ሽንፈት በመከተሉ ሳይተኮሱ የቀሩ ስንት የርችት ሳጥኖች ይኖሩ ይሆን? ሰዎች ውድ ዋጋ ከፍለው በሚመለከቱት ጨዋታ ደስታቸውን መግለጻቸው ስህተት ነው ማለት ከባድ ነው። ቶተንሃም በ1987 የኤፍኤ ካፕ ፍፃሜ ከተሸነፈ በኋላ አስቀድሞ ስለተያዘ ብቻ በአውቶቡስ አከባበር አድርጓል። በ1986 ሊቨርፑል እና ኤቨርተን በጋራ አውቶቡስ አከባበር አድርገዋል፤ ሊቨርፑል ሁለቱንም ዋንጫዎች ቢወስድም የኤቨርተን ተጫዋቾች ግን በአውቶቡሱ ውስጥ መጠጥ እየጠጡ አብረው ተጉዘዋል። የኒውዚላንድ ብሄራዊ ቡድን በ2010 የአለም ዋንጫ ሶስት ጨዋታዎችን አቻ ተለያይቶ ከምድቡ ሳይወጣ ቢቀርም “ያልተሸነፈው” የሚል ዲቪዲ ማውጣቱስ በ”አከባበር ፖሊሶች” ዘንድ ምን ያስብላል? እኔ ግን በእርግጠኝነት አየዋለሁ።
የቅርብ ጊዜው የሃሳብ ቀውሴ የመጣው የአራት ዓመት ልጄ ስለ ስርአተ ፀሐይ ካወቀ በኋላ ነው። አጽናፈ ሰማይ 14 ቢሊዮን ዓመታት ያስቆጠረ መሆኑን ስታስቡ፣ ሚካኤል አርቴታ ከቴክኒክ ቀጠናው ወጣ አልወጣ የሚለው ጉዳይ ምን ያህል ኢምንት እንደሆነ ትረዳላችሁ። በቬነስ ፕላኔት ላይ ያለው ሙቀት 465 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በሆነበት፣ ወይም በጁፒተር ላይ ለ350 ዓመታት የሚቆይ አውሎ ነፋስ ባለበት ሁኔታ፣ የእግር ኳስ ትናንሽ ድራማዎች ትርጉም ያጣሉ። ያም ሆነ ይህ፣ ነገሮችን ከትልቅ እይታ አንጻር መመልከት ጥሩ ነው። ስለዚህ መደሰት ከፈለጉ ይደሰቱ። ሰዎች በመደሰታቸው መበሳጨት ከፈለጉም ይበሳጩ። እኔ ጋር ብትመጡና የእኔ ፊት ያለበት ምንጣፍ ላይ ብትረግጡ ምንም ቅር አይለኝም።