በሌላ በኩል በ51 ሚሊዮን ፓውንድ የተፈረመው ተከላካይ አማካዩ ማኑኤል ኡጋርቴ በዚህ የውድድር ዘመን የመሰለፍ ዕድል እምብዛም አልተሰጠውም። በዚህም ምክንያት ተጫዋቹ በክረምቱ የዝውውር መስኮት በቋሚነት ሊሸጥ ወይም በውሰት ሊሰጥ እንደሚችል ተነግሯል። ኤደርሰን በጥር 2022 ከሳለርኒታና ተነስቶ አታላንታን የተቀላቀለ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ለክሩዜሮ፣ ኮሪንቲያንስ እና ፎርታሌዛ ተጫውቷል። ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን በሰኔ 2024 ከሜክሲኮ ጋር በተደረገ የወዳጅነት ጨዋታ ያከናወነ ሲሆን፣ እስካሁን ሦስት ጨዋታዎችን አድርጓል። የመጨረሻው ተሳትፎውም በመጋቢት 2025 ብራዚል በአርጀንቲና 4 ለ 1 በተሸነፈችበት ጨዋታ ነበር።
ማንቸስተር ዩናይትድ ሁለት አዳዲስ አማካዮችን ለማስፈረም ቁርጠኛ ሲሆን፣ የኤደርሰን ከአታላንታ ጋር ያለው ኮንትራት እስከ ሰኔ 2027 ድረስ ይቆያል። በዩናይትድ የዝውውር ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ሌሎች አማካዮችም አሉ፤ እነሱም ወደ 70 ሚሊዮን ፓውንድ የሚጠየቅባቸው የሪያል ማድሪዱ ኦሬሊየን ቹዋሜኒ፣ ዩናይትድ 50 ሚሊዮን ፓውንድ የገመተላቸው የብራይተኑ ካርሎስ ባሌባ፣ ቢያንስ 60 ሚሊዮን ፓውንድ የሚጠየቅባቸው የክሪስታል ፓላሱ አዳም ዋርተን እና ኖቲንግሃም ፎረስት ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በታች ድርድር የማይቀበሉባቸው ኤሊዮት አንደርሰን ናቸው። ማንቸስተር ዩናይትድ ቀጣይ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን ሰኞ ምሽት በሜዳው ከብሬንትፎርድ ጋር ያደርጋል።