በአሁኑ ወቅት የማንቸስተር ሲቲው አጥቂ ኤርሊንግ ሃላንድ 22 ግቦችን በማስቆጠር ቀዳሚነቱን ይዟል። የብሬንትፎርዱ ኢጎር ቲያጎ በ17 ግቦች ሲከተል፣ ሌላኛው የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋች አንትዋን ሴሜንዮ በ13 ግቦች ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የቼልሲው ጆአዎ ፔድሮ 11 ግቦችን ሲያስቆጥር፣ የሊቨርፑሉ ሁጎ ኤኪቲኬ እና የሊድሱ ዶሚኒክ ካልቨርት-ሌዊን እያንዳንዳቸው 10 ግቦችን በማስቆጠር ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።
የብራይተኑ ዳኒ ዌልቤክ፣ የማንቸስተር ዩናይትዱ ብራያን ምቤውሞ እና የኒውካስሉ ብሩኖ ጊማሬሽ እያንዳንዳቸው 9 ግቦች አሏቸው። በ8 ግቦች ደረጃ ላይ ደግሞ ጁኒየር ክሩፒ (ቦርንመዝ)፣ ኤንዞ ፈርናንዴዝ (ቼልሲ)፣ ኮል ፓልመር (ቼልሲ)፣ ሞርጋን ሮጀርስ (አስቶን ቪላ)፣ ዣን-ፊሊፕ ማቴታ (ክሪስታል ፓላስ)፣ ቪክቶር ግዮከሬስ (አርሰናል)፣ ኦሊ ዋትኪንስ (አስቶን ቪላ)፣ ጃሮድ ቦወን (ዌስት ሃም) እና ሃሪ ዊልሰን (ፉልሃም) ይገኛሉ።
የኒውካስሉ ኒክ ዎልቴሜድ፣ የቶተንሃሙ ሪቻርሊሰን እና የማንቸስተር ሲቲው ፊል ፎደን ደግሞ እያንዳንዳቸው 7 ግቦችን አስቆጥረዋል። በ6 ግቦች ዝርዝር ውስጥ ደግሞ ኬቪን ሻዴ (ብሬንትፎርድ)፣ ሞርጋን ጊብስ-ዋይት (ኖቲንግሃም ፎረስት)፣ ማትየስ ኩንሃ (ማንቸስተር ዩናይትድ)፣ ቤንጃሚን ሴስኮ (ማንቸስተር ዩናይትድ)፣ ብሩኖ ፈርናንዴዝ (ማንቸስተር ዩናይትድ)፣ ራውል ሂሜኔዝ (ፉልሃም)፣ ሉካስ ኔሜቻ (ሊድስ ዩናይትድ) እና ጃይደን አንቶኒ (በርንሌይ) ተካተዋል።