“በገለልተኛ ኮሚሽን በፀደቁ ሁለት የቅጣት ስምምነቶች መሰረት፣ ቼልሲ ከፋይናንሺያል ሪፖርት፣ ከሶስተኛ ወገን ኢንቨስትመንት እና ከታዳጊዎች ልማት ጋር የተያያዙ የፕሪሚየር ሊጉን ህጎች በመጣሱ በአጠቃላይ 10.75 ሚሊዮን ፓውንድ ቅጣት ተቀብሏል። ክለቡ በፕሪሚየር ሊጉ አፋጣኝ የሆነ የዘጠኝ ወራት የአካዳሚ የዝውውር እገዳ እና የአንድ ዓመት የዋናው ቡድን ተጫዋቾች ዝውውር እገዳ (ለሁለት ዓመታት የታገደ) ተጥሎበታል።”
ሊጉ ባደረገው ምርመራ እ.ኤ.አ. ከ2011 እስከ 2018 ባለው ጊዜ ውስጥ ከክለቡ ጋር ግንኙነት ባላቸው ሶስተኛ ወገኖች አማካኝነት ለተጫዋቾች፣ ላልተመዘገቡ ወኪሎች እና ለሌሎች ወገኖች ያልተገለጹ ክፍያዎች መደረጋቸውን አረጋግጧል። “እነዚህ ክፍያዎች ፕሪሚየር ሊጉን ጨምሮ በወቅቱ ለነበሩ የእግር ኳስ ተቆጣጣሪ አካላት አልተገለጹም ነበር” ሲል ሊጉ ገልጿል።
“ክፍያዎቹ የተፈጸሙት ለቼልሲ ክለብ ጥቅም ሲባል ሲሆን፣ እንደ ክለቡ ክፍያ ተደርገው ሊቆጠሩ ይገባ ነበር። ክለቡ እነዚህን ክፍያዎች መፈጸሙ እንዲሁም ለሊጉ አለማሳወቁ፣ ከሊጉ ጋር በታማኝነት የመስራት ግዴታን እንደመጣስ እንደሚቆጠር ተቀብሏል።” • ተጨማሪ ዝርዝሮች ይቀጥላሉ